የልጃገረዷ ብልህነት
በሺርጉማ ሶራጋ የተተረከ
አንዲት ልጃገረድ ከብቶች እያገደች ሳለ አንድ ሹም በአጠገቧ ሲያልፍ ስሟን ጠይቋት ነገረችው፡፡
እርሱም “ወላጆችሽ እነማን ናቸው?” ብሎ ሲጠይቃት እርሷም “እኔ የማውቃት እናቴን ብቻ ነው፡፡ አባቴን የምታውቀው እርሷ ናት፡፡” አለችው፡፡
የተከበረውም ሰው ልጅቷ የአባቷን ስም ልትነግረው እንዳልፈለገችና ክፉ እንደሆነችበት አስቦ በመበሳጨት አባቷን ወደሱ አስጠርቶ ልጁን እንዲድርለት ጠየቀው፡፡
አባቷም ልጅቷ በጣም ሃብታሙን ሹም እንድታገባውና በዚህም መስማማቱን ነገራት፡፡፡
ሆኖም ሹሙ በቀል አርግዞ ኖሮ ሁለት ስልቻ የጎመን ዘርና የጤፍበኢትዮጲያ ደጋማ ስፍራዎች የሚበቅል ሰብል ነው፡፡ ዘር በመቀላቀል ለአባትየው ልኮ ዘሮቹን እንዲለያቸው አዘዘው (ይህ በጣም አስቸጋሪ እንደሚሆን ስለሚያውቅ ይህን ማድረግ አለመቻል ምን ያህል አሳፋሪ እንደሚሆን መገመት አያዳግትም፡፡) ታዲያ ልጅቷ አባቷ ዘሮቹን እንዲዘራቸው ነግራው የጎመን ዘሩና ጤፉ በአንድ ላይ በቀሉ፡፡ ሃብታሙም ሰው ሲያይ ጎመኑና ጤፉ በቅለው አየ፡፡ የሰርጉም ቀን ደረሰ፡፡
ሁለተኛው ፈተና ደግሞ ሃብታሙ ሰው አንድ መልእክተኛ ወደ አባትየው በመላክ ልጅቷን ሲያገባት ወዲያው እንደምታረግዝና በሰርጉ እለት እንደምትፀንስ ተስማምቶ እንዲፈርም ጠየቀው፡፡
አባትየውም “ምን ባደርግ ይሻላል?” ብሎ ልጁን ጠየቃት፡፡ እርሷም “ፈርም! ግዴለህም፡፡ እኔ አንድ ብልሃት አለኝ፡፡ ለሃብታሙ ሰው ከተፈጨ ገብስ የተሰራና በሰርጋችን ዕለት የሚብላላ ጠላባህላዊ ቢራ መሰል መጠጥ አዘጋጅቶ እንድቀምሰው ከሰጠኝ ልጅ እንደምፀንስለት ንገረው፡፡” አለችው፡፡
ሃብታሙም ሰው በአንድ ቀን የሚደርስ እንደዚህ አይነቱን ጠላ ለመፈለግ ቢዋትትም ሊያገኝ ስላልቻለ መሸነፉን አመነ፡፡ “እንደዚህ ዓይነት ጠላ ማግኘት አልቻልኩም፡፡” አለ፡፡
ልጅቷም “እንግዲያው እኔም በአንድ ቀን አርግዤ እንድፀንስ እንዴት ትጠይቀኛለህ?” አለችው፡፡
ይህንንም ካለች በኋላ ተጋብተው በሰላም አብረው መኖር ጀመሩ፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|