ሰነፉ ባልና ጎበዟ ሚስት
በሺርጉማ ሶራጋ የተተረከ
አንድ የእርሻ መሬቱን ማልማት ያልቻለ ገበሬ ነበር፡፡ ወደ ጎረቤቶቹና ወደ ዘመዶቹ በመሄድ ጥራጥሬ እየለመነ ለቤተሰቡ ወደቤት ይዞ ይመጣ ነበር፡፡ በጣም ሰነፍ ስለነበረ ራሱ መስራት አይወድም ነበርና ሁልጊዜ ሲዞር ስለሚውል አንድም ቀን ቤቱ ለማደር ጊዜ ኖሮት አያውቅም፡፡
አንድ ቀን ታዲያ እቤት ያድር ዘንድ ሚስቱ ትልቅ ጥረት በማድረግ ሌሊት ወደ እርሻ ቦታው ሄዳ የእንሰትእንሰት በደቡብ ኢትዮጲያ ተፈላጊ የስር ሰብል ነው፡፡ ቁራጮችን አራርቃ ቀብራ ተመለሰች፡፡
በማግስቱ ጠዋት “ኑ! ባሌና ልጆቼ፣ አንድ ተዓምር ላሳያችሁ፡፡” አለቻቸው፡፡
ከዚያም እንሰቱን ከመሬቱ ውስጥ ቆፍራ አውጥታ አሳየቻቸው፡፡ ባሏንም “በምሳ ሰዓትም ቆፍርና እንሰት ታገኛለህ፡፡” አለችው፡፡ እርሱም ይህንን በማድረግ ለምሳ የሚሆን እንሰት አገኘ፡፡ ከዚያም “ለእራትስ?” ብሎ ጠየቀ፡፡
ሚስቱም እንሰቱን ቀብራ አርሱ አውጥቶ አብረው እራት በሉ፡፡
በማግስቱም “ሌላ ማግኘት እችላለሁ?” አለ፡፡
ሙሉ ቀንም ቆፍሮ፣ ቆፍሮ፣ ቆፍሮ እንሰት እስኪያገኝ ድረስ እየሰራና ሲደክመው እያረፈ ልጆቹም አብረውት ሲቆፍሩና እንሰት ሲያገኙ ምግብ መለመኑን አቆመ፡፡ በመጨረሻም ማሳው በሙሉ ተቆፍሮ ስላለቀ የእርሻ መሬት በመሆን ለዘር ዝግጁ በመሆኑ ቀላሉ ነገር ዘር መዝራት ብቻ ሆነ፡፡
በዚህ አይነት ሰውየው እየቆፈረ፣ ልጆቹም አብረውት እንዲቆፍሩ በማበረታታት ስራ እንዲወዱ አደረገቻቸው፡፡
< ወደኋላ |
---|