የተረገመች የእንጀራ እናት
በተሰማ ገብሬ የተተረከ
በተረቱ መጀመሪያ ላይ ተራኪው እንዲህ ይላል፤
ወማካ ኖትካ
(ተረት ልንገራችሁ)
አድማጩም እንዲህ ብሎ ይመልሳል፤
ኤጊ ኒስማሄ
(እሺ ላዳምጥህ/ሽ)
አንዲት ስምንት ወንድ ልጆችና አንድ ኮሬ የተባለ የእንጀራ ልጅ የነበሯት ሴት ነበረች፡፡ ኮሬ በጣም ጀግና ስለነበር ከጦር ሜዳ ምርኮኞች ይዞ ይመጣ ነበር፡፡ በዚህ ጀግንነቱ ስምንቱ ወንድማማቾች ይቀኑበት ነበር፡፡ እንዲገደልም ይፈልጉ ነበር፡፡ እርሱ ግን ማንም ረዳት የለውም ነበር፡፡ ስምንቱም ወንድማማቾች እንደርሱ ጀግና አለመሆናቸው እንደማያስደስታቸው ለእናታቸው ነገሯት፡፡
ወዲያውም “ለምን አናስወግደውም?” ብለው ጠየቋት፡፡
እርሷም “መልካም! እንግዲያው ወደጫካ ልኬው በዝሆን እንዲበላ አደርጋለሁ፡፡” አለቻቸው፡፡
“ይህንን ማድረግ ትችያለሽ?” ሲሏት
“አዎን እችላለሁ፡፡” አለቻቸው፡፡
ከዚህ በኋላ እናትየው ኮሬን “ልጄ ሆይ! ስለታመምኩ መድኃኒት እንድታመጣልኝ እፈልጋለሁ፡፡” አለችው፡፡
እርሱም “ምን ዓይነት መድኃኒት?” ብሎ ጠየቃት፡፡
“የዝሆን ጭራ!” ብላ መለሰች፡፡
ኮሬም በጣም ጀግና ስለነበረ ዝሆን ገድሎ ጭራውን ይዞላት መጣ፡፡ በዚህ ጊዜ እናትየውና ስምንቱ ወንድ ልጆቿ በኮሬ አለመበላት በጣም ተበሳጭተው ሊያስወግዱት ሌላ ዘዴ መዘየድ ጀመሩ፡፡
እናትየውም “አሁን ደግሞ እኔ ከወንዝ ውሃ ይዞልኝ እንዲመጣ ስልከው እናንተ አድፍጣችሁ ውሃ ውስጥ ወርውራችሁት ይሙት፡፡” አለቻቸው፡፡
ከዚያም ኮሬን “አሞኛልና በአስቸኳይ ውሃ ያስፈልገኛል፡፡” አለችው፡፡
ቀኑ መሽቶ ነበር፡፡ እርሱም ውሃውን ሊያመጣ ሲሄድ ወንድማማቾቹ ሊገድሉት ጦር ይዘው መጡበት፡፡ እርሱም ከጥቃታቸው አምልጦ አንድ በአንድ ገደላቸው፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|