ጅብና ቀበሮ (2)
በዩሱፍ አደም ማንደሬ የተተረከ
አንድ ቀን ጅብና ቀበሮ አብረው እያደኑ ሳለ አንድ የሚበላ ነገር አገኙ፡፡
ጅቡም ቀበሮውን “ይህንን ምግብ ወስደህ ደህና ቦታ አስቀምጠውና አደናችንን እንቀጥላለን፡፡” አለው፡፡
ቀበሮው ግን ሄዶ በዚያው ቀረ፡፡ በዚህ ጊዜ ጅቡ እንደተታለለ ስለገባው ቀበሮውን ይፈልገው ጀመር፡፡ ቀበሮውም ጅቡን ከሩቅ ሲያየው የሞተ በመምሰል ተዘረረ፡፡
እናም ጅቡ ቀበሮውን ሲያየው ተበሳጭቶ “አጅሬ አብረን ያገኘነውን ምግብ ጠራርገህ ከበላህ በኋላ እየተዝናናህ ነው፤ አሁን ደግሞ እኔ አንተን እበላሃለሁ፡፡” ብሎ ወደ ቀበሮው ዘለለ፡፡
ቀበሮው ግን “ተጠንቀቅ፣ እኔን ከበላኸኝ እኔን የገደለኝ ምግብ ወዲያው አንተንም ይገድልሃል፡፡” አለው፡፡
በዚህ ጊዜ ጅቡ ቀበሮው አለመሞቱን እንኳን ሳያስተውል ወደኋላው አፈግፍጎ ሮጦ ሄደ፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|