ልጆችና ዝሆኑ
በዩሱፍ አደም ማንድሬ የተተረከ
በድሮ ጊዜ ልጆች ለመፃፊያ የሚጠቀሙበት ሉህ የሚባል ከእንጨት የተሰራ የጥቁር ሰሌዳ ዓይነት ነበር፡፡ ይህም መፃፊያ ልጆቹ የሚፅፏቸው ፊደሎች ትክክል ይሆኑ ዘንድ በራሳ በሚባል መወልወያ ይወለወል ነበር፡፡ እናም በየሳምንቱ ልጆቹ በራሳ ለመልቀም ወደ ጫካ ይሄዱ ነበር፡፡ በራሳውን ካለሰለሱትም በኋላ ሉሁን ይቀቡት ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ተማሪዎቹ አስተማሪያቸውን አስፈቅደው በራሳ ለመሰብሰብ ሄደው እየለቀሙ ሳለ አንድ የዝሆን ልጅ አገኙ፡፡ የዝሆን ልጆች ከሰው ልጆች ጋር መጫወት ስለሚወዱ የዝሆኑም ግልገል ከልጆቹ ጋር ተግባብቶ መጫወት ጀመረ፡፡
ልጆቹም የዝሆኑን ግልገል ለምን በበራሳው አንወለውለውም ብለው ይወለውሉት ጀመር፡፡
ይህንንም እያደረጉ ሳለ በድንገት በራሳውን ኩምቢው ውስጥ ስለከተቱበት ግልገሉ ሞተ፡፡
ልጆቹም የዝሆኑ ግልገል መሞቱን ባዩ ጊዜ ወደ መምህራቸው ሄደው እንዲህ እያሉ ዘፈኑ “እኛ ዝሆን ገዳዮች፣ እኛ ዝሆን ገዳዮች፡፡”
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|