በአሚና መሃመድ ዋዚር የተተረከ
ነብዩ መሃመድ በፀጥታ ለመፀለይ ፈልገው ጅቡን ሄዶ የላም ግት (ጡት) እንዲያመጣ አዘዙት፡፡ ከዚያም ከፀሎት በፊት እየታጠቡ ሳለ ጅቡ በጣም በፍጥነት ሄዶ ታጥበው ሳይጨርሱ የላሟን ግት ይዞ መጣ፡፡ ነብዩም ጅቡ ፀሎታቸውን እየረበሸ ስላስቸገራቸው በጣም በመናደድ ረግመውት ሽባም ይሆን ዘንድ የጥርሳቸውን ብሩሽ ወረወሩበት፡፡
ጅቡ ታዲያ እንደድሮው ፈጣም ቢሆን ኖሮ የሰውን ልጅ በሙሉ በልቶ ይጨርስ ነበር፡፡