ፋጢማ ዚቀልና አህመድ ዚቀል
በአይ ኑሪያ ዩሱፍ አብደላ የተተረከ
ፋጢማ ዚቀልና አህመድ ዚቀል የተባሉ ሁለት እህትና ወንድም ነበሩ፡፡ የእንጀራ እናትም ነበራቸው፡፡ ታዲያ አንድ ቀን እንጀራ እናታቸው አህመድ ዚቀልን እሳት በእጁ ይዞ እንዲመጣ፣ ፋጢማ ዚቀልን ደግሞ ውሃ በወንፊት ይዛ እንድትመጣ አዘዘቻቸው፡፡ ልጁም እሳቱን በባዶ እጁ ሊያነሳ ሲሞክር አቃጠለው፡፡ እንጀራ እናት እንዴት ጨካኝ እንደሆነች ማየት ይቻላል፡፡ ፋጢማ ዚቀልም ውሃውን ለማምጣት በጣም ብትሞክርም አልቻለችም፡፡
ሁለቱም ስራቸውን እየሰሩ ሳለ ፋጢማ ዚቀል አህመድ ዚቀልን “የት ነው ያለኸው?” ብላ ተጣራች፡፡
አህመድም “እሳቱን በእጄ ለማምጣት እየሞከርኩ ነው፡፡” አላት፡፡ ከዚያም “አንቺስ የት ነሽ ፋጢማ ዚቀል?” አላት፡፡
“ውሃ በዚህ ወንፊት ለመቅዳት እየሞከርኩ ነው፡፡” አለችው፡፡
ከዚያም ፋጢማ ዚቀልና አህመድ ዚቀል ተለያይተው አንዳቸው ወደ ምስራቅ ፣ አንዳቸው ወደ ምዕራብ ለመሄድ ወሰኑ፡፡ ተለያይተውም ለረጅም ጊዜ ለየብቻ መኖር ጀመሩ፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን በአላህ ፈቃድ በመንፈስ ለመገናኘት ቻሉ፡፡
ፋጢማ ዚቀል “አህመድ የት ነው ያለኸው? ምን እየሰራህ ነው?” አለችው፡፡ አህመድም “ፋጢማ፣ እኔ እዚህ ነው ያለሁት፡፡ አንቺ የት ነሽ?” ብሎ መለሰ፡፡ ፋጢማም “እኔ እዚህ ነኝ እባክህ ወደኔ ና፡፡” አለችው፡፡
ከዚያም ተገናኝተው ስላሳለፉት ህይወት ተጨዋወቱ፡፡
በዚህ ጊዜ ጅብ መጥቶ “እናንተ እነማን ናችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው፡፡ ታሪኩን በሙሉ አጫወቱት፡፡ ጅቡም ከቀበሮ ጋር መጣላቱን ነግሯቸው እንዲያስታርቁት ጠየቃቸው፡፡ ውለታቸውንም እነርሱን በመጠበቅ እንደሚመልስ ቃል ገብቶላቸው ቀበሮዋ ስላጭበረበረችው ንብረቶች፣ ቤትና ሳንጃ እንዲሁም በሬ ዘርዝሮ ነገራቸው፡፡ ከዚያም “ፋጢማ፣ እኔ ልጅ ስላለኝ አንቺም ከእሱ ጋር መኖር ትችያለሽ፡፡ አህመድ ደግሞ ከቀበሮዋ ጋር መኖር ይችላል፡፡” አለ፡፡
ይህንንም አድርገው በደስታ አብረው መኖር ጀመሩ፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|