ሼክ ናስረዲን አህዮቹን ቆጠረ
በሃጂ አብዱሰታር መሃመድ በሽር የተተረከ
ከዕለታት አንድ ቀን ናስረዲን አህዮቹን እየነዳ ከጫካው እንጨት ሊያመጣ ሄደ፡፡ በመንገዱም ላይ አንዲቷ አህያ ላይ ተቀምጦ ሌሎቹን መቁጠር ጀመረ፡፡ አንድ፣ሁለት፣ሦስት እያለ እስከ ዘጠኝ ከቆጠረ በኋላ አስረኛዋስ? ብሎ አሰበ፣ የተቀመጠባትን አህያ መቁጠሩን ረስቶ፡፡
ከዚያም ከአህያዋ ላይ ወርዶ እንደገና ሲቆጥራቸው በዚህ ጊዜ አስር ሆኑ፡፡ ከዚያም “አሁን ልክ ነው፡፡” ብሎ ተመልሶ አህያዋን ተሳፍሮ ሄደ፡፡ እንደገና መቁጠር ሲጀምር አሁንም ዘጠኝ ሆኑበት፡፡ ለረጅም ጊዜም ግራ ከተጋባ በኋላ አንደኛዋ ለምን እያለች እንደጠፋችበት ማወቅ ተሳነው፡፡
በመጨረሻ ግን ስህተቱ ገብቶት በራሱ ሳቀ፡፡ “ሰው እንደዚህ አይነት ስህተት የሚሰራው ምን ያህል ደደብ ቢሆን ነው?”
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|