በዘይነባ አቢበከር ደረሞ የተተረከ
እባብ በዓለም ላይ እጅግ በጣም አደገኛ እንስሳ ነው፡፡ መጀመሪያ እግሮች ነበሩት፡፡ ነገር ግን እግዚእብሔር እግሮቹን ወሰደበት ምክንያቱም እግሮች ካሉት ብዙ ነገር ያጠፋልና፡፡
እንቁላል ሲጥልም በሺዎች የሚሆኑ ስለሚፈለፍል እግዚአብሔር ይህ እንዳይሆን ከለከለ፡፡ እንቁላሎቹም በከፊል አይፈለፈሉም ምክንያቱም ምድር በእባቦች እንድትጥለቀለቅ አምላክ አይፈልግም፡፡
አምላክ ጥቂቶቹ ብቻ እንዲፈለፈሉ አደረገ፡፡