አቡ ናዋስ
በዘይነባ አቢበከር ደረሞ የተተረከ
ባልና ሚስት ተጣልተው ባልየው ሚስቱን ደደብ እያለ ይሰድባታል፡፡ እሷም ጓደኞቿን “ብልጠት መግዛት እፈልጋለሁ፡፡” አለቻቸው፡፡ በዚህ ጊዜ አቡ ናዋስ ባጠገባቸው ሲያልፍ ይህንን ይሰማና ወደ ጎዳና በመውጣት መረብ ዘርግቶ ኳስ እየተጫወተና ኳሱን ወደ ላይና ወደታች በመምታት “ብልጠት የሚገዛ” እያለ ይጮህ ጀመር፡፡
እሷም “እኔ እገዛለሁ፣ ብልጠት አለህ?” ብላ ስትጠይቀው፡፡
“አዎ ልሸጥልሽ እችላለሁ፤ ነገር ግን ምን ትከፍይኛለሽ?” አላት፡፡
እሷም “የፈለከውን ነገር ልሰጥህ እችላለሁ፡፡” አለችው፡፡›
እሱም “የባልሽን ልብሶች አምጪያቸው::” አላት፡፡
እሺ ብላ የባሏን ልብሶች በሙሉ አምጥታ ሰጠችው፡፡ እሱም ኳሷን ሰጥቷት “ይህ ነው ብልጠት፡፡” አላት፡፡
ወደቤቷ በተመለሰችበትም ጊዜ ባሏ ሲመጣ “ብልጥ ገዛሁ፡፡” አለችው፡፡
“በምን ገዛሽው?” ሲላት
“ያንተን ልብሶች በሙሉ ሰጥቼ” በማለት ባሏን አበሳጨችው፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|