እሪትና ኑሪት
በዘይነባ አቢበከር ደረሞ የተተረከ
እሪትና ኑሪት የሚባሉ ሁለት ልጃገረዶች ነበሩ፡፡ እሪት ጎበዝ ስትሆን አባት እንጂ እናት የላትም፡፡ ኑሪት ጎበዝ አይደለችም፡፡ ኑሪት ሞኝ ብትሆንም ሁለቱም ወላጆቿ ግን አሉ፡፡ ታዲያ ሁለቱ ልጃገረዶች አብረው ወደጓሮ እየሄዱ የሚሸጡትን ጫትጫት በምስራቅ አፍሪካና በአረብ ባህረ ሰላጤ አካባቢ የሚገኝ የአበባ ተክል ነው፡፡ ጫት መቃም መለስተኛ መነቃቃትንና የመደሰትን ስሜት የሚፈጥር ሲሆን የማደንዘዝ ባህሪም አለው፡፡ ይለቅማሉ፡፡
ወደ ገበያ ሲሄዱ አንድ አስማተኛ ሽማግሌ ጫት እንዲሰጡት ለምኗቸው ከሰጡት እንደሚመርቃቸው ነገራቸው፡፡ እሪትም “አያቴ ሆይ ጥሩ ጫት ነው፤ ጥሩ ይሆንልዎ፡፡” ብላ ሰጠችው፡፡
ሽማግሌው ኑሪትንም ትንሽ ጫት እንድትሰጠው ለመናት፡፡
እሷም “ጫት አይደለም፣ ጎመን ነው፡፡” አለችው፡፡
እሱም “በይ ሂጂ፣ ጫቱም ጎመን ይሁን፡፡” ብሎ ረገማት፡፡
ጫቷንም ልትሸጥ ደጋግማ ብትሞክርም መሸጥ አልቻለችም፡፡ በእርግማኑ ምክንያት ኑሪትም የራሷን ጫት መሸጥ አልቻለችም፡፡ የኑሪት እናት በጣም ተበሳጭታ ስለነበር እሪትን አስራት ከመንገድ ላይ ጣለቻት፡፡ በዚህን ጊዜ አንድ የተቀደሰ በጎ አድራጊ ሰው አያት፡፡
ሰውየውም “ምን ሆነሽ ነው? ወደ ቤቴ ልውሰድሽ?” ብሎ ጠየቃት፡፡
እሷም “አዎ እሺ” ብላ ከእርሱ ጋር በመሄድ አብራው መኖር ጀመረች፡፡ በጎ አድራጊው ሰው ሊተኛ ሲል እሪትን “ጥቁር ውሃ ካየሽ አታስነሺኝ፣ ወርቃማ ውሃ ከመጣ ግን ቀስቅሺኝ፡፡” ብሏት ተኛ፡፡
ጥቁር ውሃ በመጣ ጊዜ እሪት አልቀሰቀሰችውም፡፡ ወርቃማ ውሃ ሲመጣ ግን ቀሰቀሰችው፡፡ እሱም ወርቃማ ውሃ ውስጥ አስቀምጧት ንፋሱን ጠራው፡፡
እንዲህም ብሎ አዘዘው “ከአባቷ ጣሪያ ላይ አስቀምጣት፡፡”
ከዚያ በኋላ ሞኟ ኑሪት ጠዋት ከእንቅልፏ ነቅታ ቤቱን ስትጠርግ እሪት የተፋችውን ምራቅ አየች፡፡ እሱም ወርቅ ነበር፡፡
ከዚያም ለእናቷ “እማዬ ወርቅ አገኘሁ፡፡” አለቻት፡፡
እናቷም “ጠርሙስ ውስጥ አስቀምጪው” አለቻት፡፡ አሁንም እሪት ትንሽ ምራቅ ስትተፋ ኑሪት “አሁንም ወርቅ አገኘሁ፡፡” ብላ ተናገረች፡፡ ቀና ብላ ስትመለከትም እሪትን አየቻት፡፡ እናቷንም ጠርታ “እማዬ የኛው እሪት ናት ጣሪያው ላይ ያለችው፡፡” አለቻት፡፡
የኑሪትም እናት “የቷ እሪት? በጅብ የተበላችው?” ብላ ጠየቀቻት፡፡ (ምክንያቱም እሪትን ጅብ በልቷታል ብላ ታስብ ነበር፡፡)
ከዚያ ኑሪት እሪትን “ይህን ምራቅ ወደ ወርቅነት የሚያስቀይር ስጦታ እንዴት ልታገኚ ቻልሽ?” ብላ ጠየቀቻት፡፡
እሪትም ስለ ሽማግሌው ሰው በማውሳት ታሪኩን ቀይራ ነገረቻት፡፡ እንዲህም አለቻት “ወደ እዚህ ሽማግሌ ሰው ሄደሽ ምሳውን የት መብላት እንደሚችል ሲጠይቅሽ ከመሬት ብላ በይው፡፡ እንደገናም ሽንቱን የት መሽናት እንደሚችል ሲጠይቅሽ ደግሞ መሬት ላይ ሽና በይው፡፡ በተኛም ጊዜ ጥቁሩ ውሃ ሲመጣ ቀስቅሺው፡፡”
ኑሪትም በዚህ ተደስታ እሺ በማለት ጥቁሩ ውሃ ሲመጣ ቀሰቀሰችው፡፡ በዚህን ጊዜ ሽማግሌው ጥቁሩ ውሃ ውስጥ አስቀምጧት ንፋሱን በመጥራት ልጅቷን ወደ እናቷ ማድቤት ወስዶ ከእናቷ ምጣድ ሥር ጥላሸቱ ውስጥ እንዲያስቀምጣት አዘዘው፡፡ በማግስቱ ጠዋት እናቷ ወደማድቤቱ ገብታ እሳት ልታያይዝ ስትል አንዳች ነገር ከምጣዱ ሥር አየች፡፡
ያየችው ነገር ድመት መስሏት “ክፍ ውጪ ከዚህ ቤት” ብላ ተቆጣቻት፡፡
በዚህ ጊዜ ኑሪት “እማ፣ እኔ ኑሪት ነኝ እኮ፡፡” አለቻት፡፡
ከዚያ እናቷ ከምጣዱ ስር አውጥታ በጣም ጥቁር ስለሆነች ደበቀቻት፡፡
አንድ ሰው መጥቶ እሪትን ሊያገባት በጠየቀ ጊዜ የኑሪት እናት ይህንን ስትሰማ እሪትን ወስዳ ለዘንዶ ሰጠቻት፡፡
ዘንዶውም እሪትን ውጧት ሙሽራውና ሚዜዎቹ በመጡ ጊዜ ዘንዶው ወደ እነርሱ መጥቶ “በጣም ውብና ብልህ ልጃገረድ ብሰጣችሁ ለእኔ ምን ታደርጉልኛላችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው፡፡
እነርሱም “የምትፈልገውን ነገር ሁሉ እንሰጥሃለን፡፡” አሉት፡፡ በዚህ ጊዜ ዘንዶው እሪትን ተፋት፡፡ ሙሽራውና ሚዜዎቹም እሪትን ወስደው ተጋቡ፡፡ ነገር ግን ኑሪት ውሸታም ስለሆነች ምላሷን ቆርጠው ማድቤት ውስጥ በርበሬ እንድትፈጭ አደረጓት፡፡
የዚህ ታሪክ መልዕክት ለሌላው ሰው ጥሩ ነገር የማይመኝ ሰው መጨረሻው ሁልጊዜ እንደዚህ ነው የሚል ነው፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|