ተንኮለኛው ቀበሮ
በመሃመድ አህመድ አልጋኒ የተተረከ
በአንድ ወቅት ላም ያላት ሰጎንና በሬ ያለው አንበሣ ነበሩ፡፡ አንበሳውም ሰጎኗን እንዲህ አላት፡፡ “አንቺም ላምሽን እኔም በሬዬን ለምን አብረን ወደ ግጦሽ አንወስዳቸውም? እንዲህ ካደረግን ሁለታችንም እረኝነት ከምንውል አንድ ቀን አንድ ቀን ደግሞ እኔ እየተፈራረቅን እንጠብቃቸዋለን፡፡” አላት፡፡ በዚህ ሁኔታ በኑሮዋቸው ተደስተው ለሁለት ወራት ከኖሩ በኋላ ላሚቷ ታረግዛለች፡፡
ከእለታት አንድ ቀን ታዲያ ላሚቷ መውለጃዋ በደረሰ ግዜ አንበሳው ሁኔታውን ስላየ እንዲህ አለ፡፡ “ሰጎን ሆይ! ግዴለም አንቺ አረፍ በይና ዛሬ እኔ እጠብቃቸዋለው፡፡”
ከዚያም ላሚቷ ስትወልድ አንበሳው “ያንቺ ላም ትልቅ የወፍጮ ድንጋይ የእኔ በሬ ደግሞ ጥጃ ወልደዋል፡፡”
ሰጎኗም “ይህ በጣም አስቂኝ ነገር ነው፡፡” አለች፡፡ አንበሳውም “አይደለም” አለ፡፡ በዚህም ሁኔታ ትልቅ ፀብ ውስጥ ስለገቡ ይዳኛቸው ዘንድ ሁሉንም እንስሳ ይጠሯቸዋል፡፡
ትልቅ ስብሰባም ተካሄደ፡፡ ነገር ግን ያንበሳው በሬ ጥጃ ሊወልድ አይችምል ብሎ ደፍሮ የሚናገር ጠፋ፡፡
ታዲያ አንድ ብልጣ ብልጥ ቀበሮ እንዲህ አለ፡፡ “እኔ ወደ ስብሰባው አልመጣም፡፡ ነገር ግን በፍጥነት እየሮጥኩ በስፍራው ስለማልፍ ፍርዱን እንድናገርልህ ልትጠይቀኝ ትችላለህ፡፡” በስፍራውም ቀበሮ እየሮጠ ሲያልፍ እንስሳቱ በሙሉ “አቶ ቀበሮ፣አቶ ቀበሮ፣ እባክህ ወደዚህ ና፡፡” እያሉ ተጣሩ ቀበሮውም “አልመጣም፣ እቸኩላለሁ፣ አባቴ በምጥ ላይ ስላለ ቢላዋ ይዤ እየሮጥኩ ነው፡፡ በዚህ ላይ ጀንበሯም እየጠለቀች ነው፡፡ ዝናቡም መጥቷል፣ ስለዚህ ምጥ ላይ ያለውን አባቴን ይረዱት ዘንድ ላግዛቸው ቢላዋ ይዤ እየሮጥኩ ነው፡፡” አላቸው፡፡ አንበሳውም እንዲህ አለ፡፡ “አንተ ቆሻሻ፣ አባትህ እንዴት ምጥ ሊይዘው ይችላል? ወንድ አይደለም እንዴ?”
ቀበሮውም “ስለዚህ ሌላ ቆሻሻ ነገር እንድነግርህ ትፈልጋለህ? በሬ ጥጃ ወለደ ብዬ!?” ብሎት ሮጦ ሔደ፡፡
አንበሳውም ቀበሮውን ተከትሎት ሲሮጥ ሰጎኗ ላሟንና ጥጃዋን ይዛ ሄደች፡፡
< ወደኋላ | ወደሚቀጥለው > |
---|