በወርቁ ዓለሙ የተተረከ
አንድ ልጅ አባቱን ለመርዳት የሚችለውን ሁሉ አደረገ፡፡ አባቱም ልክ ከመሞቱ በፊት ለልጁ “ያለኝ ንብረት ይህ ብቻ ነው፡፡” በማለት ትንሽ ዱላ ሰጠው፡፡ ልጁም ዱላውን ለተወሰነ ጊዜ ካቆየው በኋላ ወደ አንድ ሸለቆ ወስዶ ሲወረውረው ከአንድ የሞተ ዝሆን ላይ በማረፉ ልጁ የዝሆኑን ጥርስ ስላገኘ ሃብታም ሆነ፡፡