የኢትዮጵያ ተረቶች
(Click here for help in downloading and installing Amharic font) አብዱል ራህማን አብዱላሂ - የተረት አባት ከሃረር በዚህ ድረ-ገጽ ላይ ከእያንዳንዱ የኢትዮጵያ ክፍል እኤአ ከ1997 እስከ 2001 ዓ.ም. የተሰበሰቡ ተረቶችን ያገኛሉ፡፡ ተረቶቹ በመጀመሪያ የተሰበሰቡት ቀለል ላለ የእንግሊዝኛ ንባብ መጽሃፍት ለማዘጋጀት ሲሆን ይህም ህጻናት ተማሪዎች በየክልላቸው ባህላዊ እሴቶች ላይ ተመስርተው የተጻፉትን ተረቶች ማንበብ እንዲችሉና በዚያውም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታቸውን እንዲዳብሩ በማሰብ ነው፡፡ በአጠቃላይ እንደነዚህ ያሉ ስምንት የንባብ መጽሃፍት ተዘጋጅተዋል፡፡ ይህ ድረ-ገጽ የተዋቀረው በፕሮጀክቱ ሂደት ወቅት የተሰበሰቡትን የበለጸጉና ልዩ ልዩ ተረቶች ለሰፊው አንባቢ ተደራሽ ለማድረግ ነው፡፡ እነዚህ ተረቶች ከጥንት ጀምሮ ኢዮጵያውያን እርስ በርስ ሲተራረኩዋቸው የኖሩ ድንቅ ሃብቶች ሲሆኑ ብዙዎቹ ከዚህ በፊት በጽሁፍም ሆነ ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ ተተርጉመው የሚገኙ አይደሉም፡፡ ተረቶቹ የተሰበሰቡት በትምህርት ሚኒስቴርና በብሪቲሽ ካውንስል የበላይ ተቆጣጣሪነትና በኢትዮጵያ ክልላዊ የባህልና ትምህርት ቢሮዎች ተባባሪነት ኤልሳቤት ላየርድ በተባሉ ተረት አሰባሳቢ ነው፡፡ ሁሉም ተረቶች በእንግሊዝኛ ተጽፈው ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ብዙዎቹን ተረቶች በተለያዩ ሁኔታዎችና ባልተዋጣለት መሳሪያ በመስክ ላይ ተራኪዎቹ ሲተርኳቸው የተቀዳውን ኦሪጂናል ድምጽ ማዳመጥ ይችላሉ፡፡ አብዛኛዎቹ ተረቶች የተተረኩት በአማርኛ፣ ጥቂቶቹ ደግሞ በእንግሊዝኛ ቢሆንም ሌሎች በተለያዩ ቋንቋዎች ማለትም በኦሮምኛ፣በሶማሊኛ፣በአኙዋክ፣በጉሙዝና በኑዌር ቋንቋዎች የተተረኩም አሉ፡፡ ቅጂዎቹ የሚሰሙት በቅደም ተከተል ሲሆን አሁን ባሉበት ሁኔታ ቅጂዎቹን ከጽሁፎቻቸው ማዛመድ አልተቻለም፡፡ የተረቶቹም ቅደም ተከተል ሁልጊዜ ላይዛመድ ይችላል፡፡ ተራኪዎቹ፤ ሴቶቹንና ወንዶቹን ጨምሮ አመጣጣቸው ከተለያዩ የባህል፣ የቋንቋና ማህበራዊ ዳራዎች ነው፡፡ ከነዚህም ውስጥ አርሶ አደሮች፣ መምህራን፣የጤና ባለሙያዎች፣ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ተማሪዎች፣ ባለ ሱቆች፣ የቀድሞ ወታደሮች፣ አንዲት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እማሆይ፣ ቄስና በጡረታ የተገለሉ ዲፕሎማት የገኙባቸዋል፡፡ ከዚህ ድህረ-ገፅ በተጨማሪ የእንግሉዘኛ ቋንቋ ችልታችሁን ይበሌጥ ሇማሻሻሌ የሚያግዙ 88 (ሰማኒያ ስምንት) ተረቶች ተመርጠውና በደረጃ ተሇይተው በላሊ ድህረ-ገፅ ቀርበውሊችኋሌ፡፡ በእያንዳንዱ ተረት ግርጌም የእንግሉዘኛ ቋንቋ ግንዛቤያችሁን ሇመመዘን የሚያስችለ ጥያቄዎች ቀርበዋሌ፡፡ በተጨማሪም እያንዳንዱ ተረት እንግሉኛ ቋንቋ አፍ መፍቻቸው በሆኑ ሰዎች በንባብ (ድምፅ) የቀረቡ ስሌሆነ ማዳመጥ ይቻሊሌ፡፡ ይሄንን በጣም ጠቃሚ የሆነ የእንግሉዘኛ መማሪያ ፅሑፍ ሇመከታተሌ ይሄንን ድህረ-ገፅ ተመሌከቱwww.ethiopianenglishreaders.com. ተረቶች ከዋና ዋና ባህላዊ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ሃብቶች መካከል ተጠቃሽ ናቸው። ስለሆነም የዚህ ድረ-ገጽ ዓላማ እነዚህን የህብረተሰብ ቅርሶች እንዲታቀቡ ለማድረግ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለእያንዳንዱ ሰው እንዲዳረሱ ለማገዝም ጭምር ነው። ከዚህ በተጨማሪ ልዩ የእትዮጵያ ቅርስ የሆኑትን፡ ብርቅየ አገር በቀል ተክሎችንና እንሰሳትን፡ እንዲታቀቡ ማድረግ እጅግ በጣም አስፈላጊ ስራ ነው። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማህበር ዓላማም ይህን የተቀደሰ የአገር ሃብት እንዲታቀብ ለማገዝ የተመሰረተ ማህበር ነው። በአሁኑ ወቅት የዚህ ማህበር ዋነኛ ፕሮጀክት የሆነው የእንጦጦ የተፈጥሮ ፓርክ ነው። ማህበሩ ከተመሰረተ ከ 1995 እ ኤ አ ወዲህ ከ600 000 (ስድት መቶ ሽህ) በላይ አገር በቀል ዛፎችን በ 13 ስኩወር ኪሎ ሚትር የፓርኩ ቦታ ላይ እንዲተከል አድርጉዋል። ቀደም ሲል ይህ ቦታ ከውጭ መጥ በሆነ የባህር ዛፍ ተክል የተሸፈነ ነበር፡፡ ማህበሩ የጀመረውን ያገር በቀል ዛፎች ተክልን መንከባከቡንና ማስፋፋቱን በይበልጥ በመቀጠል ላይ ይገኛል። |
|