Ethiopian Folktales

The Three Misfitsሶስቱ አልተግባብቶዎች

Tigrayትግራይ

Text size Share

Narrator Unknown

There were three men. One is bald. The other has a rash from being dirty. The third is full of phlegm.

They agree that they have special characters, “So let’s go together.”

They start going together and the dirty nose says, “When an airplane passes, it says, ‘Whoo!’” While he says this he blows his nose.

The dirty-skinned one clasps his hands and says, “Oh, one day I saw two goats fighting like this.” In fact he’s scratching his sores.

The bald one says, “What liars you are,” covering his bald head with his hands.

ሶስቱ አልተግባብቶዎች

ተራኪው የማይታወቅ

ሶስት ሰዎች ነበሩ፡፡ አንደኛው ራሰ በራ ነበር፡፡ ሁለተኛው ከመቆሸሹ የተነሳ እከክ ይዞት ነበር፡፡ ሶስተኛውም ንፍጣም ነበር፡፡

እነዚህም ሰዎች ልዩ ባህሪያት እንዳላቸው ተስማምተው “ስለዚህ አብረን እንሂድ፡፡” ተባባሉ፡፡
አብረውም እየሄዱ ሳለ ንፍጣሙ ሰውዬ “አውሮፕላን ሲያልፍ ‘ሁሁሁ,,,,,,,’ ይላል፡፡” ብሎ የአውሮፕላኑን አስተላለፍ ያሳየ በመምሰል አፍንጫውን ይጠርጋል፡፡

እከካሙም ሰው እጆቹን በማቆላለፍ “ኧረ አንድ ቀን ሁለት ፍየሎች እንደዚህ እያደረጉ ሲጣሉ አየሁ፡፡” ብሎ የፍየሎቹን ፀብ ያሳየ መስሎ ቁስሉን ያካል፡፡

ራሰ በራውም “ምን አይነት ውሸታሞች ናችሁ!” ብሎ የተገረመ በመምሰል መላጣውን በእጆቹ ሸፈነ ይባላል፡፡