Ethiopian Folktales

The Hyena, the Fox and the Monkey 2ጅብ፣ ቀበሮና ጦጣ 2

Tigrayትግራይ

Narratorተራኪ: Unknown

Text size Share

Narrator Unknown

The hyena, the fox and the monkey were living together and one day they kidnapped four cows from one of the houses in the village. They took one each and one remained.

“What shall we do with the fourth?”

They discussed it.

“They said, “Let the oldest one take the fourth.”

So they agreed and they asked the hyena, “When were you born?”

He said, “Last year and before last year.”

The monkey answered, “I was born when the sky and the earth were made.”

The fox says, “That’s right. I remember. I heard a grey-haired man was born and I attended the ceremony and I had wheat porridge, cakes with butter and berberi{footnote}Very hot Ethiopian red pepper.{/footnote} in his gellop.” ( A ceremony of clothes washing after seven days after birth.)

“So who is the oldest?”

The fox.

So she took the fourth cow.

ጅብ፣ ቀበሮና ጦጣ 2

ተራኪው የማይታወቅ

ጅብ፣ ቀበሮና ጦጣ አብረው ይኖሩ ነበር፡፡ ታዲያ ከእለታት አንድ ቀን አራት ላሞችን በመንደሩ ካለው አንድ ቤት ሰረቁ፡፡ እያንዳንዳቸው አንድ፣ አንድ ላም ከተካፈሉ በኋላ “አራተኛዋን ላም እንዴት እናድርጋት” ብለው ተወያዩባት፡፡

ከዚያም “አራተኛዋን ከሁላችንም በእድሜ አንጋፋ የሆነው ይውሰዳት፡፡” አሉ፡፡

በዚህም ከተስማሙ በኋላ ጅቡን “መች ነው የተወለድከው?” ብለው ሲጠይቁት “አምናና ካቻምና፡፡” አላቸው፡፡

ጦጣውም “እኔ የተወለድኩት ሰማይና ምድር ሲፈጠሩ ነው፡፡” አለ፡፡ ቀበሮዋም “ትክክል ነው፡፡ አስታውሳለሁ፡፡ አንድ ሽበታም ሰው መወለዱን ሰምቼ በድግሱ ላይ ተሳትፌ የስንዴ ገንፎ፣ ኬክ በቅቤና በርበሬ{footnote}በርበሬ በጣም የሚያቃጥል የኢትዮጵያ ቅመም ነው፡፡{/footnote} በጌሎፑ ላይ በልቻለሁ፡፡” አለች፡፡ (ጌሎፕ ልጅ ከተወለደ ከሰባተኛው ቀን በኋላ የሚደረግ የልብስ አጠባ ስርአት ነው፡፡)

“እና አንጋፋው ማነው?”

ቀበሮዋ፡፡

እናም እርሷ አራተኛዋን ላም ወሰደች፡፡