Ethiopian Folktales

Mother Fox and the Hyenaእናት ቀበሮና አያ ጅቦ

Tigrayትግራይ

Text size Share

Narrator Unknown

There was a fox with her two cubs. She gave a name to one of them: Weynai, which means not too bright, not too black.

When the fox goes to the field to collect food she closes the door with the cubs inside. The other cub is Gella.

When the fox comes back, she says:

"One Weynai

One Gella

Open the door for me."

One day, when she calls her cubs, the hyena hears. So when the fox goes hunting, the hyena comes and calls the same way. The cubs hesitate because the voice is different. The hyena changes his voice and makes it thinner and says the same words. Now they believe it’s their mother and open the door. He eats them.

The fox comes home. When she calls her usual cry, no answer comes. She jumps into the house and she knows they’ve been eaten by the hyena.

The next day she prepares a hole in the ground and covers it with goatskin and invites the hyena to share a sheep.

“Come, eat.”

The hyena comes and she says, “Sit on the goatskin.”

But the hyena sees the goatskin sink a bit into the hole.

“Oh it’s nothing. Sit there.”

So he sits on it and falls through. The fox takes boiling water and pours it on to him.

እናት ቀበሮና አያ ጅቦ

ተራኪው የማይታወቅ

አንዲት ሁለት ግልገሎች የነበሯት ቀበሮ ነበረች፡፡ አንደኛውን ልጇን ወይናይ ብላ ሰየመችው፡፡ (ይህም ማለት እምብዛም ያልፈካና እምብዛም ያልጠቆረ ማለት ነው፡፡)

ቀበሮዋም ምግብ ፍለጋ ስትሄድ ግልገሎቿን ዘግታባቸው ትሄድ ነበር፡፡ የሌላኛው ግልገል ስም ጌላ ነበር፡፡

ቀበሮዋም ወደቤቷ ስትመለስ እንዲህ ትላለች፤

አንድ ወይናይ 

አንድ ጌላ

በሩን ክፈቱልኝ፡፡

ታዲያ አንድ ቀን ቀበሮዋ ልጆቿን ስትጣራ አያ ጅቦ ይሰማና ቀበሮዋ ወደ አደን ስትሄድ እናታቸውን አስመስሎ ጠራቸው፡፡ ግልገሎቹ ግን ድምፁ ስለተለየባቸው ተጠራጠሩ፡፡ በዚህ ግዜ ጅቡ ድምፁን የበለጠ አቅጥኖ የጥሪ ቃላቱን ሲደግም እናታቸው መስላቸው በሩን ሲከፍቱ ጅቡ በላቸው፡፡

ቀበሮዋም ወደቤቷ ተመልሳ በተለመደ ድምጿ ልጆቿን ብትጣራ መልስ አጣች፡፡ ወደ ቤቱ ውስጥም ዘላ ስትገባ ግልገሎቹ በጅቡ እንደተበሉ አወቀች፡፡

በሚቀጥለው ቀን ታዲያ ቀበሮዋ ጉድጓድ አዘጋጅታ ጉድጓዱን በፍየል ቆዳ ከሸፈነችው በኋላ ጅቡን አንዲት በግ ከእርሷ ጋር ተካፍሎ እንዲበላ ጋበዘችው፡፡

“ና ብላ፡፡” ብላ ስትጠራው ጅቡ በመጣ ጊዜ “የፍየሉ ቆዳ ላይ ተቀመጥ፡፡” አለችው፡፡

ነገር ግን ጅቡ የፍየሉ ቆዳ ወደጉድጓዱ ውስጥ በመጠኑ ጎድጎድ ማለቱን አየ፡፡ ቀበሮዋ ግን “ኧረ ምንም አይደል! እዚያ ተቀመጥ፡፡” ስትለው አያ ጅቦ ቆዳው ላይ ሲቀመጥ ወደ ጉድጓዱ ውስጥ በወደቀ ጊዜ ቀበሮዋ የፈላ ውሃ ጨምራበት ሞተ፡፡