Ethiopian Folktales

Celebrating the Revolutionየአብዮት በዓል

Amharaአማራ

Text size Share

Narrated by Shimelash Bequele

There was a man called Kumche Ambau who was a government official in Buwi during the Dergue1 period. He is famous for celebrating the fourth anniversary of the revolution by lighting forty candles. Later on he was transferred from Buwi to Machakel as a government official. In Machakel one elementary school teacher wanted to take annual leave and asked Kumche Ambau (the government official) to give him leave. Kumche Ambau asked the teacher to answer the following question as a criterion to have the permission and forgetting that it is his right to take leave.

“Who celebrated the fourth anniversary of the revolution by lighting forty candles?”

The teacher answered, “That’s simple. It is the great Comrade Kumche Ambau.”

And Kumche Ambau allowed him six months leave without any legal basis.

የአብዮት በዓል

በሽመላሽ በቀለ የተተረከ

በደርግ1 ጊዜ የቡዊ ወረዳ አስተዳዳሪ የነበረ አንድ ቆምጨ አምባው የተባለ ሰው ነበር፡፡ አራተኛውን የአብዮት በዓል 40 ሻማ አብርቶ በማክበር ይታወቃል፡፡ በኋላም ከቡዊ ወደ መተከል ተዛውሮ በመሥራት ላይ ሣለ አንድ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር ቆምጨ አምባውን የዓመት ፈቃድ እንዲሰጠው ይጠይቀዋል፡፡

ቆምጨ አምባውም የዓመት እረፍት መውሰድ የመምህሩ መብት መሆኑን ዘንግቶ ፈቃዱን ለማግኘት አንድ ጥያቄ መመለስ እንዳለበት ይነግረዋል፡፡

”አራተኛውን የአብዮት በዓል 40 ሻማ አብርቶ ያከበረው ማነው?” ብሎ ሲጠይቀው መምህሩም “ይህማ ቀላል ነው:: ያ ሰው ታላቁ ጓድ ቆምጨ አምባው ነው፡፡” ብሎ ሲመልስለት ቆምጨ አምባውም ያለምንም ህጋዊ ማስረጃ የስድስት ወር ፈቃድ ሰጠው፡፡

In the original voice — hear tales from Amharaአማራ, told in Amharic. Listen ›