The Woman and the Lionሴቷና አንበሳው
Benishangul-Gumuzቤንሻንጉል-ጉሙዝ
Narrated by Fatima Ali
There was a woman who was mistreated by her husband. He always beats her. She does everything he wants. She brings his injera1 and wat2 but he always beats her. This woman was very much in a problem.
“I always do what he wants, but still he beats me. What shall I do?”
From time to time she went on asking advice from neighbours, relatives etc, and she was very much disturbed.
They tell her, "Go there, go here. Somebody might give you are remedy. There is a medicine there. There is a medicine here."
She went to a wise man.
“What’s the matter?”
She told him, “I do everything my husband says, I give him what he wants, but he beats me. He mistreats me. I couldn’t get any remedy for this.”
“There is no remedy here,” he says. “I can’t give you any medicine. If you can get the eyebrows of the lion, bring them to me. I will do something for you.”
She was at first very much afraid.
“How can I get the eyebrows of a lion?”
She killed a goat.
“Maybe doing this I can get the eyebrows of the lion.”
She sits on a tree where the lion cannot get her.
The first day, she killed the goat and threw a big piece to the lion. She did this seven days continuously. After doing this repeatedly, the lion ate the flesh and drank water at the foot of the tree. After the seventh day, she threw a bit of a stick at him while he was dozing to check on him if he would wake up. He didn’t wake.
“Now, that is my time to get the eyebrows.”
She climbed down the tree and took the eyebrows and went. Then she went to the wise man.
“How did you bring it?”
“Well, for seven days I took the flesh of the goat and threw it to the lion and while he was asleep that’s how I got it from him.”
The wise man answered, “Therefore it is just like this that you can win your husband, otherwise there is no remedy. Be as tactful as he wants you to be."
ሴቷና አንበሳው
በፋጡማ አሊ የተተረከ
ባሏ የሚበድላት አንዲት ሴት ነበረች። ሁልጊዜም ይደበድባት ነበር። የሚፈልገውን ሁሉ ብታደርግለትም፣ እንጀራና ወጥ ብታቀርብለትም ሁልጊዜ ስለሚደበድባት በጣም ትቸገር ነበር።
“ሁልጊዜ የሚፈልገውን ነገር ሁሉ አደርግለታለሁ፤ እርሱ ግን ሁልጊዜ ይደበድበኛል፤ ምን ባደርግ ይሻለኝ ይሆን?” ብላ ታማርር ነበር።
በየጊዜው ከጎረቤቶቿ፣ ከዘመዶቿ ወዘተ… ምክር ብትጠይቅም በጣም ትረበሽ ነበር።
እነርሱም “እዚህ ሂጂ፣ እዚያ ሂጂ፤ እዚያ መድኃኒት አለ፣ እዚህ መድኃኒት አለ፤ መፍትሔ ታገኛለሽ” እያሉ ይነግሯት ነበር።
አንድ ብልህ ሰው ዘንድም ሄደች።
እርሱም “ችግርሽ ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቃት።
እሷም እንዲህ አለችው፦ “የሚፈልገውን ሁሉ ባደርግለትም፣ የሚፈልገውን ነገር ሁሉ ብሰጠውም ባሌ ሁልጊዜ ይደበድበኛል፤ ለዚህ ምንም መፍትሔ ማግኘት አልቻልኩም።”
እሱም “እዚህ ምንም መፍትሔ የለም፤ ምንም ዓይነት መድኃኒት ልሰጥሽ አልችልም። ከቻልሽ ግን የአንበሳ ቅንድቦች ብታመጪልኝ አንድ ነገር አደርግልሻለሁ” አላት።
ይህንን ስትሰማ መጀመሪያ በጣም ፈራች።
“የአንበሳ ቅንድብ እንዴት ላገኝ እችላለሁ?” ብላ አሰበች። ከዚያም አንዲት ፍየል ከገደለች በኋላ ‘በዚህ ዓይነት የአንበሳ ቅንድብ ማግኘት እችል ይሆናል’ ብላ አሰበች።
አንበሳ ሊያገኛት ከማይችልበት ዛፍ ላይ ወጥታ ተቀመጠች። በመጀመሪያውም ቀን ፍየሏን ገድላ ትልቅ ሥጋ ለአንበሳው ወረወረችለት። ይህንንም በተከታታይ ለሰባት ቀናት አደረገች። አንበሳውም በተደጋጋሚ የሚወረወርለትን ሥጋ እየበላና ከዛፉ ሥር ያለውን ውሃ እየጠጣ ቆየ። በሰባተኛውም ቀን አንበሳው ከእንቅልፉ ይነቃ እንደሆነ ለማየት አንዲት ቁራጭ እንጨት ብትወረውርበትም አንበሳው አልነቃም።
“እንግዲህ ቅንድቦቹን የማገኝበት ጊዜው አሁን ነው” ብላ ከዛፉ በመውረድ ቅንድቦቹን ወስዳ ሄደች። ወደ ብልሁ ሰው ዘንድም አመራች።
“እንዴት ልታመጪ ቻልሽ?” ብሎ ጠየቃት።
“ለሰባት ቀናት ያህል የፍየል ሥጋ ስወረውርለት ቆይቼ፣ በመጨረሻውም ቀን እንቅልፍ ሲጥለው ቅንድቦቹን ወሰድኩ” አለችው።
ብልሁም ሰው “ታዲያ ባልሽንም የምታሸንፊው ልክ እንደዚህ ነው፤ ሌላ መፍትሔ የለውም። እሱ እንደሚፈልገው በመሆን በዘዴ ያዢው” አላት ይባላል።
(ማብራሪያ፦
- እንጀራ ብዙውን ጊዜ ከጤፍ የሚሠራ ክብና ጠፍጣፋ ምግብ ነው።
- ወጥ ከእንጀራ ጋር የሚቀርብ ማባያ ነው።)
In the original voice — hear tales from Benishangul-Gumuzቤንሻንጉል-ጉሙዝ, told in Berta, Shinasha, Gumuz. Listen ›