The Fruit of the Landየምድሪቷ ፍሬ
Amharaአማራ
Narrated by Worku Mersha
There was somebody called Kenjazmach1 Sewnate who lived in Debre Marcos, capital of Gojjam2. He used to enjoy tej3, and he sold his land.
When asked why he sold his land, he said, “I shall eat the fruit of the land before the land eats me.”
And he sold a eucalyptus4 tree before it was full grown.
When asked why, he said, “I don’t want to get thin while it’s getting thick.”
የምድሪቷ ፍሬ
በወርቁ መርሻ የተተረከ
የጎጃም1 ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው ደብረ ማርቆስ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ አንድ ቀኝ2 አዝማች ሰውነቴ የተባሉ ሰው ነበሩ፡፡ እሳቸውም ጠጅ3 በጣም ይወዱ ነበርና እርስታቸውን ሸጡ፡፡
መሬታቸውን ለምን እንደሸጡ በተጠየቁም ጊዜ “ምድሪቷ ሳትበላኝ በፊት የምድሪቷን ፍሬ ልብላ ብዬ ነው፡፡” ብለው መለሱ፡፡
ባህርዛፉንም4 በለጋነቱ ሸጡት፡፡ አሁንም ለምን እንዲህ እንዳደረጉ ሲጠየቁ “እሱ እየወፈረ እኔ መክሳት አልፈልግም፡፡” ብለው መለሱ ይባላል፡፡
In the original voice — hear tales from Amharaአማራ, told in Amharic. Listen ›