Ethiopian Folktales

The Girl’s Wisdomየልጃገረዷ ብልህነት

Gurage Zoneጉራጌ ዞን

Text size Share

Narrated by Shirguma Soraga

A girl was looking after cattle when a shum (a kind of governor) passed by. He asked her name and she told him.

“Who are your parents?” he asked next.

“I know only my mother. She knows my father.”

The nobleman was angry, thinking she was rude because she didn’t want to tell him her father’s name. He had the father brought to him. He asked the father for his daughter’s hand.

The father told the girl she was going to marry the shum, a very wealthy man. The father had already agreed.

But the shum wanted to play a revenge game. He sent two sacks of mustard and tef1 seeds mixed together to the father and he told him to separate them (this would result in humiliation because he could not do it). The girl told him to sow the seeds. The mustard and tef grew. The wealthy man saw it – this is the mustard, this is the tef. So the wedding day came.

The second test was, the wealthy man sent a messenger to the father to sign that when he marries the girl she must get pregnant at once and bear a child that same day.

“What shall I do?” he asked her.

“Sign it. Don’t worry,” his daughter said. “I have an idea. Send this message to the wealthy man. If you can prepare a tala2 whose barley is ground, which ferments on the very day of our wedding and give me so I can taste it, I can bear you a child.”

So he went everywhere looking for such a tala and he couldn’t find one, so he gave in.

“I can’t find one.”

She said, “Then how can you expect me to conceive and bear a child in one day?”

So saying, they got married and lived happily ever after.

የልጃገረዷ ብልህነት

በሺርጉማ ሶራጋ የተተረከ

አንዲት ልጃገረድ ከብቶች እያገደች ሳለ አንድ ሹም በአጠገቧ ሲያልፍ ስሟን ጠይቋት ነገረችው፡፡

እርሱም “ወላጆችሽ እነማን ናቸው?” ብሎ ሲጠይቃት እርሷም “እኔ የማውቃት እናቴን ብቻ ነው፡፡ አባቴን የምታውቀው እርሷ ናት፡፡” አለችው፡፡

የተከበረውም ሰው ልጅቷ የአባቷን ስም ልትነግረው እንዳልፈለገችና ክፉ እንደሆነችበት አስቦ በመበሳጨት አባቷን ወደሱ አስጠርቶ ልጁን እንዲድርለት ጠየቀው፡፡

አባቷም ልጅቷ በጣም ሃብታሙን ሹም እንድታገባውና በዚህም መስማማቱን ነገራት፡፡፡

ሆኖም ሹሙ በቀል አርግዞ ኖሮ ሁለት ስልቻ የጎመን ዘርና የጤፍ1 ዘር በመቀላቀል ለአባትየው ልኮ ዘሮቹን እንዲለያቸው አዘዘው (ይህ በጣም አስቸጋሪ እንደሚሆን ስለሚያውቅ ይህን ማድረግ አለመቻል ምን ያህል አሳፋሪ እንደሚሆን መገመት አያዳግትም፡፡) ታዲያ ልጅቷ አባቷ ዘሮቹን እንዲዘራቸው ነግራው የጎመን ዘሩና ጤፉ በአንድ ላይ በቀሉ፡፡ ሃብታሙም ሰው ሲያይ ጎመኑና ጤፉ በቅለው አየ፡፡ የሰርጉም ቀን ደረሰ፡፡

ሁለተኛው ፈተና ደግሞ ሃብታሙ ሰው አንድ መልእክተኛ ወደ አባትየው በመላክ ልጅቷን ሲያገባት ወዲያው እንደምታረግዝና በሰርጉ እለት እንደምትፀንስ ተስማምቶ እንዲፈርም ጠየቀው፡፡

አባትየውም “ምን ባደርግ ይሻላል?” ብሎ ልጁን ጠየቃት፡፡ እርሷም “ፈርም! ግዴለህም፡፡ እኔ አንድ ብልሃት አለኝ፡፡ ለሃብታሙ ሰው ከተፈጨ ገብስ የተሰራና በሰርጋችን ዕለት የሚብላላ ጠላ2 አዘጋጅቶ እንድቀምሰው ከሰጠኝ ልጅ እንደምፀንስለት ንገረው፡፡” አለችው፡፡

ሃብታሙም ሰው በአንድ ቀን የሚደርስ እንደዚህ አይነቱን ጠላ ለመፈለግ ቢዋትትም ሊያገኝ ስላልቻለ መሸነፉን አመነ፡፡ “እንደዚህ ዓይነት ጠላ ማግኘት አልቻልኩም፡፡” አለ፡፡

ልጅቷም “እንግዲያው እኔም በአንድ ቀን አርግዤ እንድፀንስ እንዴት ትጠይቀኛለህ?” አለችው፡፡

ይህንንም ካለች በኋላ ተጋብተው በሰላም አብረው መኖር ጀመሩ፡፡

In the original voice — hear tales from Gurage Zoneጉራጌ ዞን, told in Gurage. Listen ›